Tuesday, December 17, 2013

በጅጅጋ የተካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ማለፉ በክልሉ ሰላም አለመኖሩን ያመለክታል ሲሉ አንድ ታዛቢ ተናገሩ

በመንግስት የሀላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አንድ ስማቸው እንዳይገለጸት የፈለጉ ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በክልሉ በቆዩባቸው ቀናት የታዘቡት ነገር ቢኖር በክልሉ የሰላም እጦት ዋናው ችግር መሆኑን ነው።

ምንም እንኳ መንግስት ያለምንም ችግር በአሉ መጠናቀቁን ቢገልጽም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ እንደነበር ሃላፊው ይናገራሉ። በከተማዋ ዳርቻዎች ታንኮች፣ ከባድ መሳሪያ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ፣ ልዩ ኮማንዶችና እና እስካፍንጫቸው የታጠቁ እግረኛ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላት የ24 ሰአታት ጥበቃ ሲያደርጉ ፣ ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች ደግሞ የአየር ላይ ቅኝት ያደርጉ ነበር። ጥበቃው እስከ አዋሳኝ ወረዳዎች ዘልቆ እንደነበር የገለጹት ሀላፊው፣ መኪኖች በበአሉ ዝግጅት ወቅት እንዳይንቀሳቀሱ ታግተው እንደነበር ገልጸዋል።  የበአሉ አከባበር በስታዲየሙ ውስጥ ብቻ ይካሄድ እንደነበር የገለጹት እኝሁ ሀላፊ፣ ሌላው የጅጅጋ ክፍል የሞት ከተማ ይመስል ነበር ሲሉ አክለዋል። በጦርነት ቀጠና ውስጥ እንኳ ቢሆን፣ በዚህ አይነት ወታደራዊ ጥበቃ ማንኛውንም አይነት በአል ማክበር እንደሚቻል የገለጹት ባለስልጣኑ፣ አካባቢውን የጎበኙ የውጭ አገር ዜጎችና ሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸው   ሰላም በኢህአዴግ እይታ ምን ማለት እንደሆነ በቂ ግንዛቤ ወስደዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በበአሉ ላይ ለመሳተፍ እንግድነት ተጠርተው ከሄዱት እንግዶች መካከል የኬንያውና የሩዋንዳው አፈ-ጉባኤዎች ተቀባይ አጥተው ሲቸገሩ እንደነበር እኝሁ ሀላፊ ተናግረዋል። የኬንያው አፈጉባኤ የተጋበዙት በአባ ዱላ ገመዳ ሲሆን፣ የሩዋንዳው ደግሞ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉበኤ ካሳ ተክለብርሀን ነበር። ይሁን እንጅ ሁለቱ ልኡካን ጅጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቶ አባ ዱላም ሆኑ አቶ ካሳ ተክለብርሀን አልተቀበሉዋቸውም፣ እነሱን የሚቀበል ሌላ ሰውም አላዘጋጁም። ልኡካኑ ግራ ተጋብተው በጅጅጋ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከቆዩ በሁዋላ፣ የጅጅጋ ፖሊስ በአንድ አሮጌ ፒክ አፕ የፖሊስ መኪና አሳፍሮ ጅጅጋ ሆቴል እንዲያርፉ አድርጓል። ልኡካኑ እንዲያርፉ የተደረገበት ሆቴል ደረጃውን የማይመጥን ነበር ሲሉ ባለስልጣኑ ገልጸዋል። የልኡካን ቡድኑ በመጡበት ወቅት አባ ዱላና አቶ ካሳ ተክለብርሀን በተዘጋጀላቸው የእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ በመዝናናት ላይ ነበሩ።
ልኡካኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሄደው ባለመቀበላቸው ማዘናቸው ሳያንስ በተያዘላቸው ሆቴል እጅግ ተበሳጭተው ነበር።  የሶማሊ ክልል አስተዳደር የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ለውጭ አገር እንግዶች ተገቢውን ክብር ባለመስጠታቸው ማዘኑን መግለጹም ታውቋል።

የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተመሰረተበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

ታህሳስ 7  2006 ዓም የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከተመሰረተ  አንድ አመት ሞላው። አንድ አመት  በጭንቅና  በአሳር  ለተያዘች የዛሬይቱ ኢትዮጵያና ህዝቧ እጅግ ረጅም ግዜ እንደሆነ ህዝባዊ ሃይሉ በሚገባ  ይገነዘባል። ባላፈው አንድ አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ የመከራ የአሳርና የውርደት ህይወት ይበልጥ እየሰፋ፣ የሚፈጸምበት ግፍ ይበልጥ እየገዘፈ መሄዱን አይተነዋል። በሃገርና በህዝብ ላይ እየወረደ ያለውን ወያኔ ወለድ የስቃይና የፍዳ ናዳ በቅጡ ላጤነው  ሃገሪቱና ህዝቧ የአዳዲስ የስቆቃና የመከራ አይነቶች መፈተኛ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ለመሆኑ ጥርጥር አይኖረውም። ለሚራበው ለሚረገጠው በግፍ ለታጎረው፣ በኑሮ ውድነት ለሚጠበሰው፣ ለተሰደደው ለተፈናቀለው ኢትዮጵያዊ እንድ አመት በሲኦል የቀናትና የወራት መቁጠሪያ እንደሚለካ ዘመን እጅግ የረዘመ የስቃይ ግዜ ነው።

Ginbot 7 Popular Force logo
የዋልድባ መነኩሳት ገዳማችን  አትድፈሩ አታፍረሱ በማለታቸው እየተገረፉ ለዘመናት ፈጣሪያቸውን ከሚማጸኑበት ለሃገርና  ለህዝብ ምልጃ ከቆሙበት ገዳም በዘር መመዘኛ እየተለዩ  እንደቆ ሻሻ ተጠርገው የተባረሩበት ፣ እምነታችን አትንኩ ያሉ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  መሪዎቻቸው በሃሰት ክስ ተመስርቶባቸው  ወህኒ መውረዳቸው አንሶ  ወንድሞቻችን ይፈቱ በማለት  ሰላማዊ  ጥያቄ ያቀረቡ ወገኖቻቸን በወያኔ ነፍሰ- ገዳዮች  በአረመኔያዊ ጭካኔ የተጨፈጨፉት በዚሁ አመት ነው። ወያኔ በህዝብ መሃከል በዘራው የዘር መርዝ የተነሳ በሽዎች የሚቆጠሩ አማሮች ከጉራ ፈርዳና ከቤንሻንጉል፣ ኦሮሞዎች ለዘመናት ከኖሩበት ምስራቅ ሃረርጌ  አካባቢ  እንዲፈናቀሉና በገዛ ሃገራቸው መድረሻ ቢሶች  እንዲሆኑ የተደረገው በዚህ አንድ አመት ውስጥ ነው። ጋምቤላዎች ሙርሲዎች አፋሮችና ሌሎችም ብሄረሰቦችና ማህበረሰቦች የተጨፈጨፉበት፣በልማት ስም ለመጡ የውጭ ወራሪዎችና ወያኔ ለፈጠራቸው ቱጃሮች ቦታ እንዲለቁ ተደርጎ ቀደምቶቻቸው ለዘመናት ከኖሩባቸው ቀየዎች እንዲነቀሉ ተደርገው እንደ አልባሌ ነገር የትም እንዲበተኑ የማድረጉ ሂደት ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ የቀጠለው በዚሁ አመት ነው። በዚሁ አንድ አመት በወያኔ የሃገሪቱ ገዥዎች በህዝብ ላይ የተፈጸመው  ጭካኔና ወንጀል ተዘርዝሮ  የሚያልቅ አይደለም።
ይህ ወያኔ  ሰራሽ ሃገር በቀል የውርደትና  የስቃይ ህይወት አልበቃ  ብሎ ወያኔ ከሳውዲ የጨለማ ዘመን ገዥዎች ጋር በመተባበር ወንድሞቻችን በሳውዲ አውራ ጎዳናዎች ላይ እንዲታረዱ እህቶቻችን በቡድን በተደራጁ የሳውዲ ጎረምሳዎች  እንዲደፈሩ ሁኔታዎችን አመቻችቶ  ለኢትዮጵያውያን ያለውን እጅግ የከረረ ጥላቻ በአደባባይ ያሳየበት አመት ነው። እንዲህ አይነቱ የጅምላ ግፍና  ውርደት ከመከሰቱ በፊት ህዝባዊ ሃይሉ በአረብ ሃገር በባርነትና  በስደት የሚገኙ እህትቶቻችንን ወንድሞችችን ስቃይ  ስቃዩ አድርጎ በመውሰድ “ላንቺ ነው” በሚለው ድርጅታዊ መዝሙሩ “በባለጌ  አረቦች መዳፍ ውድ ክብራቸው ለጎደፈው እህቶቻችን፣ በአረቦች የባርነት ቀንበር ጀርባቸው ለጎበጠው  ወገኖቻችን እንደርስላችኋለን፣ የተሰባሰብነው  ደማችን የሚፈሰው የመከራ ቀናችሁን ለማሳጠር ነው” የሚል ቃል ኪዳኑ ሰጥቶ  ነበር። የድርጅታችንን ምስረታ አንደኛ  አመት ስናከብር ልባችንን ደስታ ሳይሆን ሃዘን እንዲሞላ የሚያደርገው ይህ ቃል ኪዳናችን ለማክበር የጀመርነው ጉዞ ከድርጅት ምስረታና ከድርጅታዊ ዝግጅት አልፎ   በኢትዮጵያ ህዝብ ጥላቻና ንቀት  የተነፋውን የወያኔን እብሪት በማስተንፈስ የወሰዳቸው ተጨባጭ የአለኝታነት እርምጃዎች ባለመኖራቸው ነው።
ምንም እንኳን ግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል እራሱን እንደ ድርጅት አቁሞ  ኢትዮጵያውያንን አሰባስቦ  መራራው ትግል የሚጠይቀውን የፖለቲካ  የወታደራዊ ስልጠናና ትጥቅ አስታጥቆ  በወያኔ  ላይ ለመዝመት የጀመረውን ጉዞ የሚያስቆመው ምድራዊ ሃይል እንደሌለ ብናውቅም የህዝብ ስቃይ ለግዜው መቀጠሉ የህባዊ ሃይሉን አባላት ማሰቃየቱ አልቀረም። በወያኔ  ግፈኛ አገዛዝ የተንገፈገፈው ወገናችን ህዝባዊ ሃይሉ የወያኔን አገዛዝ እድሜ  የሚያሳጥሩ ፈጣን እርምጃዎችን እንዲወስድ በከፍተኛ  ጉጉት እየተጠባበቀ እንደሆነ  እናውቃለን። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች በተጠንቀቅ እንደቆሙ እናውቃለን። እነዚህ ዜጎች ከሁሉም የእምነት የቋንቋ  የጾታ የእድሜ  የኑሮና  የማህበረሰብ ስብጥር የሚያካተቱ  እንደሆኑ እናውቃለን። በሃገሪቱ ታሪክ ተሰምቶና  ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ  የወታደር ልብሱን  እየጣፈ እንዲለብስ፣  የወታደር ጫማውን መቀየሪያ አጥቶ  ሸበጥ እንዲያደርግ የተገደደውን፣  የወያኔ ጀነራሎች በስልጣንና  በዘረፋ ሲያብጡ በድህነት እንዲሟሽሽ የተፈረደበት የሃገሪቱ ሰራዊት በዘር በእምነት ሳይለያይ ከህዝባዊ ሃይሉ ጎን ለመቆም አሰፍስፎ  የቆመ  እንደሆነ  እናውቃለን። ይህ ሃገራዊ እውነታ ለህዝብ የገባነውን ቃልኪዳን የለምንም ጥርጣሬ  ማስከበር እንደምንችል በሙሉ ድፍረት እንድናውጅ የሚያስችለን ሃቅ ነው።
የወያኔ ጀንበር እየጠለቀች የኢትዮጵያ  ህዝብ ጀንበር እየፈካች የመሄዱ ጉዳይ እንደማይታጠፈው  የመንጋትና  የመምሸት የተፈጥሮ ህግ ነቅነቅ የማይል እንደሆነ ግንቦት7 ጠንቅቆ ያውቃል።  እውቀታችን ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ ኣይደለም። ግፍ ፍትህን አሸንፎ፣ እውነት በሃሰት ተደፍቃ፣ ጥላቻ ፍቅርን፣ አድሎ እኩልነትን፣ ሃገራዊ ክህደት ሃገር መውደድን፣ ባንዳነት አርበኛናትን ለዘላላሙ ቀብረው የሄዱበት የሃገራችንና  የሰው ልጆች ታሪክ የለምና የወያኔን አይቀሬ ሞት ለመተንበይ  ልዩ ጥበብ አያሻንም። ይህን እኛ ብቻ ሳንሆን በዘረፋና በጥላቻ  የደነዘዘ ህሊና ያዳበሩት የወያኔ  ባለስልጣናትም ያውቁታል። ያለእኔ  ጀግና የለም፣ ያለእኔ  አልሞ  ተኳሽ የለም በሚል እብሪት በመጻደቅ የሚታወቁት ወያኔዎች በመቶ ሽዎች በሚቆጠሩ ወታደሮች ተከበው፣  በታንክ በአይሮፕላን በሚሳይል ታጅበው ከሚኖሩበት ቤተመንግስትና ቪላዎች ውስጥ ብርክ እንዲይዛቸው ያደረገው ለመሆኑ፣  ሳር ቅጠሉ ግንቦት ሰባት እየመሰላቸው ሲበረግጉ እንደሚያመሹ፣  የግንቦት ሰባት አባላት እያሉ ከድርጅታችን ጋር አንዳችም ግንኙነት የሌላቸውን ዜጎች እያሰሩ ሲያሰቃዩ ፣  ከምላሳቸው ላይ ግንቦት 7  የሚል ስም ተፈናጦባቸው  እንደሚውሉ በራሳቸው ሚድያ  ወያኔዎች ራሳቸው እያሳዩን እያስደመጡን ነው። ከዚህም አልፎ በዚህ አንድ አመት ውስጥ  የህዝባዊ ሃይሉን መሪዎች በመግደል ድርጅቱን ለማኮላሸት ይቻላል በሚል ወያኔ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮችና ድርጅቱን ከውስጥ ለመቦርቦር ያሰማራቸው ሰርጎገቦች ተራ በተራ ተልእኳቸው እየከሸፈ በህዝባዊ ሃይሉ እጅ እየወደቁ ወይም ተልእኳቸው እንደማይሳካ ሲረዱ እየፈረጠጡ ወደ ወያኔ ሲመለሱ አይተናል።
ያለፈው አንድ አመት ተመክሯችን ስለወያኔ  ብቻ ሳይሆን ስለራሳችንም ጥንካሬና  ድክመት ብዙ ነገሮች ያስተማረን ኣመት ነው። የቀደምቶቻችን የጀግንነት የአርበኛነት ቅርስ በመላ ህዋሳቸው የተሸከሙ  ለኢትዮጵያ እና  ለህዝቧ ሲሉ ደማቸው ለማፍሰስ ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት ወደኋላ የማይሉ ቆራጥ ብቻ ሳይሆኑ አርቀው የሚያዩ  በርካታ ልጆች  ሃጋሪቷ ያሏት መሆኑን ያረጋገጥንበት አመት  ነው።  በሌላ በኩል ደግሞ  ድርጅታችን የኢትዮጵያን ህዝብ ብቸኛው የመንግስት ስልጣን ባላቤት የማድረጉን ታሪካዊ ራእዩን ለመሳካት የሚያደረገው ትግል ከወያኔ ጋር ብቻ ሳይሆን ከራሳችንም ጋር የሚደረግ እንደሆነ  በሚገባ  የተረዳነው  በዚሁ የአንድ አመት የድርጅታችን እድሜ  ነው። ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል ወያኔ በማህበረሰባችን ውስጥ ከዘራቸውና የሃገሪቱን ዜጎች እንዲበክሉ ካደረጋቸው የዘረኛነት የአድሎ  ከህዝብና  ከሃገር ጥቅም በፊት የራስን ጥቅም ማስቀደም፣ የሱሰኛነትና የሙስናና ሌሎችም አደገኛ ባህሎች ጋር ነው።
ህዝባዊ ሃይሉ ደግሞ  ደጋግሞ  እንደገለጸው ትግላችን አንድ መንግስታዊ ስርአት ወድቆ ሌላው የመንግስት ስርአት በመጣ ቁጥር የህዝብ ተስፋ እየጨለመ  “አዲስ ከመጣው ስርአት ያላፈው ያረጀ ስርአት በግፈኛነቱ በዘራፊነቱ ያነሰ ነበር” የሚል የግፈኛና የዘራፊ ስርአቶች ንጽጽር ላይ የቆመ አሳዛኝ የህዝብ ህይወት እንዲያበቃ ነው። ደርግን ያየ የአጼውን ስርአት እንከኖች ረስቶ ንጉሱ ይሻሉን ነበር ያለበት፣ ወያኔን ያየ የደርግን አስከፊ ዘመን ረስቶ መንጌ በስንት ጣሙ ያለበት አሳዛኝ ሁኔታ ከወያኔ መውደቅ በኋላ በሃገራችን እንዳይደገም ነው ትግላችን። የኢትዮጵያ ህዝብ የውድ ልጆቹን ህይወት ገብሮ ወያኔን በማስወገድ የሚያመጣው ስርአት ከወያኔ ብሶ ህዝብ ወያኔ ማረኝ የሚልበትን ቅስም ሰባሪና አዋራጅ የታሪክ ቅጥልጥሎሽ  እንዳይቀጥል ማድረግ ህዝባዊ ሃይሉ የተመሰረተበት፣ አባላቱ መከራ ለመቀበልና መስዋእትነት ለመክፈል በረሃ የገቡበት ዋናውና ብቸናው ምክንያት ነው። ትግላችንን መራራ የሚያደርገው ከበሰበሰውና የአንድ ጀምበር የህዝብ ቁጣ ከታሪክ ቆሻሻ የመጠያ ስፍራ ከሚከምረው  የወያኔ ስርአት ጋር ብቻ ሳይሆን በወያኔ ቦታ የሚተካውን ስርአት ከአድሎና ከዘረኛነት ከዘረፋና ሃገራዊ ክህደት የጸዳ፣ ዳግም ለኢትዮጵያውያን ውርደትና እንግልት ምክንያት እንዳይሆን ለማድረግ ከራሳችን ጋር ሳይቀር የማያቋርጥ ትግልን ማድረግ የግድ ስለሚል ነው። ህዝባዊ ሃይሉ የአመጽ ትግል የሚያደርግ፣ የመሳሪያው ብዛትና  የሰራዊቱ ቁጥር እያደገ  የሚሄድ ሃይል መሆኑን ስለምንረዳ  ይህን ሃይል ገና ከጅምሩ ከብዙ እንከኖች እያጸዱ ማደራጀት ካልተቻለ  በሃገርና በህዝብ ላይ የሚመጣውን አደጋ  የህዝባዊ ሃይሉ አባላት ጠንቅቀው የተረዱት ሃቅ ነው። ይህ ግንዛቤ የሰራዊቱን አባላት በጥንቃቄ መመልመልን፣ ማሰልጠንንና መገንባትን የግድ የሚል ነው።
ይህ ከራሳችን ጋር የሚደረግ ትግል እጅግ መራራ ነው። ታሪካዊ ስህተቶችን ላለመድገም የሚደረግ ትግል ነው። ይህ ትግል የአካልና የመንፈስ ጽናትን፣ ሃቀኛነትን፣ ታማኝነትን፣ ጀግንነትን የሚጠይቅ ትግል ነው። የወያኔ ስርአት ከሃገር ግድያው በተጨማሪ ትውልድን ለመግደል ሆን ብሎ ያስፋፋቸው እኩይና ጎጂ ባህሎችና ልምዶች ምን ያህል ማህበረሰባችንን እንደጎዱት ህዝባዊ ሃይሉ ባላፈው አንድ አመት እድሜው በሚገባ የተረዳው ጉዳይ ሆኗል። ህዝባዊ ሃይሉ የሚመኘውን የኢትዮጵያ ትንሳኤና ተሃድሶ እውን ለማድረግ እነኝህ  ወያኔ ሆን ብሎ  ያስፋፋቸውን የባህልና የሞራል ብክለት ማጽዳት የግድ እንደሆነ የተረዳ አካል ሆኗል።
ትግላችን መደፍረስን መጥራትን፣ መንተክተክን መስከንን የትግሉ ሂደት አካል አድርጎ  የሚጓዝ ነው።   ትግሉ የሚልመጠመጠውን እንደቀስት ቀጥ ብሎ ከሚራመደው፣ በካፊያው የሚንቀጠ ቀጠውን ለዶፉ ደንታ ከሌለው፣ ዝናር በቅፌን ከምሩ ተኳሽ  የሚለይ መራራ ትግል ነው። ያለፈው አንድ አመት ይህን አስተምሮናል። ህዝባዊ ሃይሉ ትግሉ ቀላል ነው የሚል ከእውነታ ጋር ያልተያያዘ ቃል ለህዝብም ሆነ ህዝባዊ ሃይሉን ሊቀላቀሉት ለተዘጋጁት ወገኖቹ አይናገርም። ህዝባዊ ሃይሉን ለመቀላቀል ለተሰለፉ በሽዎች ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ትግሉ የሚጠየቅውን የሞራል የስብእና ጥብቅነት፣ከፍተኛ  የሃገርና የወገን ፍቅር፣ ጥልቅ የሆነ የመስዋእትነት ፈቃደኛነት የሚጠይቅ መሆኑን ከማስረዳት አንቦዝንም። ህዝባዊ ሃይሉ ለህዝብ ቃል እንደገባው ከወያኔ  ጋር የምናደርገው ትግል በጥበብ በእውቀት በጥናት በጥንቃቄ የምናደርገደው ነው። ነጻነት ያለመስዋእትነት እንደማይሳካ ብናውቅም ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። የውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።
ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ የድርጅት ምስረታ  መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ  ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ነው። በዚህ ረገድ የተሰራው ስራ አጥጋቢ ውጤት አስገኝቷል። ስልጠናው፣ ድርጅት ማጠናከሩና  ማጥራቱ ወደፊትም የሚቀጥል ነው። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሃይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባላፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የሃገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት አመት መሆኑ ነው። በዚህ የህዝባዊ ሃይላችን የአንደኛ አመት ምስረታ  ክብረ በአል ወቅት ወገንም ጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ብቻ ነው።
ውድመት ለዋናውና  ለብቸኛው የኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያችን ጠላት ለሆነው የወያኔ ገዥ ጉጅሌ!
ድል በወያኔ ግፈኛ ስርአት አበሳውን ለሚያየው የመላው የኢትዮጵያ  ህዝብ!

Sunday, December 8, 2013

የአፄ ምኒልክ 100 ኛ ሙት-ዓመትና ክንዋኔዎቻቸው

አውሮፓውያን ከዚያ በፊት ያልታዬ ከእርስ -በርስ አስከፊ ፍጅት የደረሱበት የአንደኛው የዓለም ጦርነት ሊፈነዳ 7 ወራት ገደማ ሲቀሩት ነበረ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ታኅሳስ 3 ቀን 1906 ዓ ም ያረፉት።
minilik
በዘመኑ ብቸኛይቱን አፍሪቃዊት ነጻ ሀገር ይመሩ የነበሩት አፄ ምኒልክ ህዝባቸውና የጦር አለቆቻቸውን አስተባብረው ፣ መላ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ሥር ለማድረግ የዘመተውን የኢጣልያ ጦር ኃይል አድዋ ላይ ድል በመምታት ፣ በዘመኑም የዘመናዊ ሥልጣኔ መገለጫዎች የነበሩ ስልክና ባቡር ሐዲድ በማስገባት ፣ ት/ቤትና ባንክ የመሳሰሉትን ተቋማት በመክፈት ይታወቃሉ። በውጭው ዓለም የተፈሩ ፣ የተከበሩ ፣ በቅኝ ግዛት ሥር ለነበሩ አፍሪቃውያንና ከባህር ማዶ ፣ በካሪቢያን ደሴቶችና በሰሜን አሜሪካ፣ ለአፍሪቃ ዝርዮች እንደ ነጻነት አባት፤ ሀገራቸውም የጥቁር ህዝብ አለኝታ ሆና ትታይ ነበር። ከጦርነት ይልቅ፤ ውዝግቦችን በሰላም፤ በዘዴ ፣ መፍታትን ይመርጡ የነበሩት ንጉሠ-ነገሥት፣ ሉዓላዊ ግዛት በመመሥረቱ ረገድ፣ በዓለም ታሪክ ውስጥ የተለዬ ነገር ባያደርጉም፤ ካረፉ ከ 100 ዓመታት ወዲህም፣ ብዙዎች የሚወዷቸውንና የሚያደንቋቸውን ያክል የሚወቅሷቸውና የሚከሷቸውም አሉ። አጼ ምኒልክና ክንዋኔዎቻቸው በታሪክ እንዴት ይመዘናሉ?በዛሬው እንወያይ፣ የዳግማዊ አፄ ምኒልክን 100ኛ ሙት ዓመት መነሻ በማድረግ፤ ክንዋኔዎቻቸውን ፤ ውርሳቸውን በአጭሩ እንቃኛለን። 3 እንግዶች ጋብዘናል።
ተክሌ የኋላ
ልደት አበበ
Source/www.dw.de.com

ሚሚ ስብሃቱ ጠረጴዛ ምን ያደርግላታል?


ከዳዊት ሰለሞን
ጠረጴዛ ከመመገቢያነት፣ለመጻፊያ ማስደገፊያነትና ከቁሳቁስ ማስቀመጫነት በተጨማሪ በዙሪያው በሚኮለኮሉት ወንበሮች የተነሳ ሰዎችን በአንድነት መሰብሰብ በመቻሉ የሐሳብ መንሸራሸሪያ መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡ ግለሰቦችና ቡድኖች በፊት ለፊታቸው በተዘረጋው ጠረጴዛ ላይ ሐሳባቸውን፣አመለካከታቸውንና አይዶሎጂያቸውን ያቀርባሉ፡፡የተጣሉ፣ልዩነት ያለባቸው ወገኖችም በጠረጴዛ ዙሪያ ቅራኔያቸውን ለማጥበብ ይደራደራሉ፡፡

ሚሚ ስብሃቱ ከቪኦኤ መልስ በታደለችው ዛሚ ራዲዩ ጣቢያ አማካኝነት ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ››የተባለ መርሃ ግብር ታዘጋጃለች፡፡በሚሚ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲታደሙ የሚፈቀድላቸው ወይም በቋሚነት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸው‹‹በጠረጴዛው››የተወሰነ መሆኑም ድንቅ ይለኛል፡፡

ጋዜጠኞቹ ሚሚ ስታሽካካ አብረዋት የሚያሽካኩ የራሳቸው ሳቅ ወይም ለቅሶ የሌላቸው ‹‹እንገላበጥ››በማለት የሚጠይቁ ሁሌም ባለችው ላይ የሚጨምሩ መሆናቸውም ‹‹ጠረጴዛው››እውነት ከብበውታልን በማለት እንድጠይቅ ያደርገኛል፡፡

ሚሚ ዳዊት ከበደ መታሰር ይገባዋል ካለች ቀሪዎቹ የጠረጴዛው ታዳሚዎች‹‹እስካሁን አለመታሰሩ እንደሚገርማቸው ያክላሉ፣አንድነት ፓርቲ የግንቦት 7 ትርፍራፊን ለማግኘት ይሰራል ካለች አጃቢዎቿ ‹‹ለዚህ እኮ ነው የጸረ ሽብር አዋጁ ይሰረዝ የሚለው ይላሉ፡፡
ዛሬ አንድ ወዳጄ ደውሎ ሚሚን ስማት አለኝ፡፡ወሪያቸው ሚስ አና ጎሜዝን የተመለከተ ነበር ፡፡ሚሚ የስድብ መዝገበ ቃላቷን ጠረጴዛዋ ላይ ከፍታ ፖርቹጋላዊቷን የሰብዓዊ መብት ታጋይና የአውሮፓ ፓርላማ አባል ታወርድባታለች፡፡አና ሚሚን ባትሰማትም ሚሚ በተሳደበች ቁጥር ማንነቷን የምትገኝበትን ስብዕና የበለጠ እመለከት ነበር፡፡ማን ነበር ሰው አፉን ሲከፍት ሆዱ ይታያል ያለው፡፡

ሚሚ አና ጎሜዝ ወደ አገራችን እንድትገባ በመደረጓ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አዝነዋል፡፡ብላለች የእርሷ ብዙ ስንት እንደሆነ ባይገባኝም፡፡አና ለሚዲያዎች በሰጧቸው ቃለ ምልልሶች መለስን መረር ባሉ ቃላቶች መግለጻቸው ሚሚን አንጨርጭሯታል፡፡እንዲህ በመናገሯ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ተቆጥተዋል ከማለትም አልተመለሰችም ‹‹መለስ መላጣ ብሎ ማንም ሊሰድበኝ ይችላል መላጣዬን ግን እንዲነካ አልፈቅድለትም››ማለታቸውን ሚሚ እንዴት እንደረሳቸው አልገባኝም፡፡አና መለስን ‹‹አጭበርባሪ ነበር››በማለት ገልጸውታል፡፡አያጭበረብርም የሚል ካለ አናን መሞገት እንጂ‹‹እንዴት ብሎ በጠረጴዛ ዙሪያ የስድብ መዓት ማዝነብ የሚቻል አይመስለኝም ፡፡

አና መለስን እንዲህ ያሉት ከመሬት ተነስተው አልነበረም፡፡ያው ምርጫ 2005ን ማስታወስ ብቻ ይበቃል፡፡እነ ሚሚ የመለስን የቲና ተርነር ዘፈን በማስታወስም ወይዘሮዋ ብርሃኑ ነጋ ጋር ስለነበራቸው ግኑኝነት ለመሳለቅ ሞክረዋል፡፡እንግዲህ አና በዘንድሮው የአዲስ አበባ አመጣጣቸው ደመቅ ያሉ ፎቶ ግራፎችን ከአባ ዱላ ገመደና ከተሾመ ቶጋ ጋር ተነስተው ተመልክተናል፡፡አና አባዱላን ወይም ተሾመን አፈቀሩ ወይስ ሁለቱ ሰዎች አናን ከብርሃኑ ነጠቁ?

እነሚሚ ይህንን ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ከዚህ ይልቅ ተዘባዝበው አድማጮቻቸውን ተሰናበቱ፡፡እኔ ልጠይቅ በዛሚ ጠረጴዛ የሚሰባሰቡ ሰዎች አንድ አይነት ዘፈን የሚዘፍኑ ሚሚ ያለችውን እንደ በቀቀን የሚደግሙ እንደ ገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ ናቸው፡፡ታዲያ ጠረጴዛ ምን ያደርግላቸዋል፡፡ባዶ ቤት አይሻልም፡፡ለእስክስታውም ይመቻል ብዬ እኮ ነው፡፡

ተማሪዎች ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ነው!

ከ2005 አጋማሽ በኋላ የአወልያ ግቢን መሰረት ያደረገውንና 2004 ታህሳስ ወር የተጀመረውን የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረከብ እንዳለባቸው የሚያስረዱ ጥሪዎች ከየአቅጣጫው ይሰሙ ጀመር፡፡ ይህ አስፈሪ አቅጣጫ ልቦናው ውስጥ ከፍተኛ ፍርሀት የፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በራሳቸው ጉዳይ (በሰላትና ሂጃብ ጉዳይ) እንዲጨናነከትሎ በጥር ወር 2005 መጀመሪያ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊኖር የሚገባውን የቁ በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ እንዳይሳተፉ ለመግታት ማሰቡን ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የወጣ መረጃ አመለከተ፡፡ ይህን ውሳኔ ተአለባበስ፣ አመጋገብና አምልኮ ስነ-ስርአት አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አውጥቶት የነበረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ረቂቅ ደንብ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ተግባራዊ አደረገ፡፡ ይህ ገና በውይይት ላይ የሚገኝ ረቂቅ ደንብ ምንም እንኳ ሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚመለከት ቢመስልም ቅሉ ግን ያነጣጠረው ድሮም በእናት አገሩ ኢትዮጵያ ፍዳውን እያየ በኖረው ሙስሊም ተማሪ ላይ ነበር፡፡ በውስጡም ሂጃብንና ሰላትን የሚገድቡ ህገ ወጥ ኢህአዴጋዊ ሴራዎች የተጎነጎኑበት ነበር፡፡
በሂደትም 13 የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኒቃብ ለባሽ እህቶች በይፋ እንዲባረሩ ተደረገ፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመዓ አጠቃላይ አሚር ተባረረ፡፡ በወቅቱ የተፈጠረውን ውዝግብ ያባብሳሉ ተብለው የሚታሰቡ 12 ሙስሊም ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተለጠፈላቸው፡፡ በግቢው የጀመአ ሰላት የሚሰገድባቸው ንብረቶች ተዘረፉ፡፡ ኒቃባቸውን አውልቀው እንዲማሩ፣ ወይም ዊዝድሮዋል ሞልተው ወደቤታቸው እንዲሄዱ፣ አለበለዚያ ግን እንደሚባረሩ አስከፊ ምርጫ የተሰጣቸው ሙተነቂብ እህቶች ‹‹አናወልቅም፤ እንማራለን›› በማለታቸው በዩኒቨርሲቲው ፖሊሶችና የተማሪዎቸ የመኝታ አገልግሎት ሀላፊዎች ከነሻንጣቸው እንደባእድ ከግቢው ውጭ ተወረወሩ፡፡ ተሰብስበው ሲሰግዱ የታዩ 28 ሴት ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ጭራሽ ‹‹100 ሜትር ተራርቃችሁ መስገድ አለባችሁ›› እስከመባልም ተደረሰ!
የረቂቅ ደንቡን ህገ ወጥነት ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሀይማኖታዊ ድንጋጌዎች አንጻር፣ ከአለም አቀፍ ህግጋት አኳያ፣ ኢትዮጵያ ‹‹ፈለጋቸውን ተከትያለሁ›› ከምትላቸው ሴኩላር አገራት ተሞክሮ አንጻር፣ እንዲሁም ለሰላትና ሂጃብ ኢስላም ከሚሰጠው ቦታ አንጻር መንግስት ባዘጋጃቸው የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ያስረዳው መላው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ (ክርስትያኖችንም ይጨምራል) በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህገወጥ እርምጃ ቁጣውን መግለጽ ጀመረ፡፡ ጾም፣ ፔቲሽን፣ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ፣ ሌላም ሌላም ተደርጎ በዩኒቨርሲቲው ተቃውሞ ተጧጧፈ፡፡
ቁጥራቸው ከ700 እስከ 1200 የሚደርሱ የባህር ዳር ሙስሊም ተማሪዎች ‹‹ሃይማኖታችን እስትንፋሳችን በመሆኑ ካለሱ መኖር አንችልም!›› በማለት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡ የዚህ ሁሉ የተማረ ሀይል ትምህርት መስተጓጎል ያላሳሰበው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር (መንግስት) ‹‹ሰላት ኦክስጅናችን ነው ብለዋል፤ እስቲ ይሞቱ ከሆነ እናያለን!›› ብሎ ከማሾፍ አንስቶ ተመልሰው ትምህርታቸውን የማይቀጥሉ ከሆነ ለተፈጠረው ችግር ሀላፊነቱን እንደማይወስድ፣ ‹‹አንዳንድ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለማስተዳደር ያወጣውን ደንብ አንቀበልም በማለት ትምህርት ማቋረጣቸው ይታወቃል›› የሚል የተጻፈበትን ዛቻ አዘል ማስታወቂያ በመለጠፍ ድሮም አላማቸው የተማረውን ሙስሊም ወጣት ከትምህርት ማደናቀፍ መሆኑን አሳበቀ፡፡
በዚህ ክስተት ማግስት ነው እንግዲህ የተማሪዎች እስር የተጀመረው፡፡ መንግስት በየዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ተቃውሞ (የህዝበ ሙስሊሙንም የተማሪውንም) ‹‹እያቀጣጠሉብኝ ነው›› ብሎ ያሰባቸውን 17 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አንድ ሌክቸረር ከየዩኒቨርሲቲው በመልቀም የግፍ ማእከሉ በሆነው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) በየተራ አጎራቸው፡፡ በምርመራው ሂደትም ‹‹ፖሊስ›› ተማሪዎቹን ‹‹ሁሉንም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት ያለሙ ናቸው፤ ምናልባትም ከግብጽና ሳኡዲ መንግስት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው አይቀርም፤ ግብረ አበሮቻቸው ከኢትዮጵያ የወጡ በመሆኑ መንግስት ከጎረቤት አገሮች ጋር ተነጋግሮ ለመያዝ በውይይት ላይ ነው፤ የቴክኒክ ማስረጃዎችን እያሰባሰብን ነው፤ ሂደታቸው በፍርድ ቤት እየታየላቸው ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ራእይና አላማ ለማስቀጠል ሲንቀሳቀሱና ተማሪውን ለሁከት ሲያነሳሱ የነበሩ ናቸው፤ ተማሪዎችን ለጂሀድ ጦርነት ሲያዘጋጁ ነበር…›› ወዘተ በማለት ቀኑን ሙሉ ያለከልካይ በሚፈነጭበት አራዳ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከሶ ለአራት ወራት ሲያመላልሳቸው ቆይቷል፡፡
ከአራት ወራት የምርመራ ቆይታ በኋላ አምስቱ (4 ወንድ 1 ሴት) ተለቀው 13ቱ ደግሞ (12 ወንድና 1 ሴት) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የሽብርተኝነቱን አንቀጽ በመቀየር የወንጀል ህጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፣ 38/1 እና 257/ሀ ተላልፈዋል በማለት ከሷቸዋል፡፡ እንግዲህ ልጆቹ ሽብርተኛ ሳይሆኑ ነው ያን ያህል ካንገላቷቸው በኋላ የሽብርተኝነት ክሱን የተዉት! አዲሱ ክሳቸው በጥቅሉ ‹‹የትምህርት ሚኒስቴርን ረቂቅ ደንብ ተግባራዊነት አደናቅፈዋል፤ ራሳቸውን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በማለት የሰየሙትን ግለሰቦች በሃይል ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል›› የሚል ሆነ፡፡
በሂደት 4ኛ ወንጀል ችሎት ይህንን ጉዳይ የማየት ስልጣን የሌለው መሆኑን ገልጾ በ14ኛ ወንጀል ችሎት በአንድ ዳኛ ብቻ እንዲታይ ተደረገ፡፡ ተማሪዎቹም እንደህግ የተከሰሱበት አንቀጽ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው ተፈቅዶ ጉዳያቸውን በውጪ እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱን ጠየቁ፡፡ እጅግ የሚገርሙ ትርኪ ምርኪ ምክንያቶችን በመደርደር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ለመወሰን ብቻ 15 የሚደርሱ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል፡፡ በምሳሌነት ብናይ፡-
*ሰኔ 10-10-2005 ‹‹የክስ መቃወሚያ እንስማ›› በሚል ለዋስትና ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ፤
*ሰኔ 17-10-2005 ‹‹አልደረሰልንም፤ ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?›› ተባለ፤
*ሰኔ 19-10-2005 ‹‹አልደረሰልንም፤ ሌላ ሪፈር የምናደርገው ነገር አለ›› ተባለ፤ (የአለቆቹን እነ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያምን ተጽእኖ ሪፈር ለማድረግ ይሆን?)
*በሌላ ቀጠሮ ደግሞ ‹‹በቃ በሚቀጥለው ሳምንት ቁርጣችሁን እናሳውቃችኋለን›› ተብሎ ተቀጠረ፤
*ሐምሌ 05-11-2005 ‹‹ከምስክር ጋር አብረን እናየዋለን›› ተባለ፤
በዚህ መልኩ ብዙ እንዲመላለሱ ከተደረገ በኋላ ከ2005 የኢድ ተቃውሞ በኋላ በነበራቸው ቀጠሮ አቃቤ ህግ ‹‹ልጆቹ የተያዙበት እንቅስቃሴ አሁንም በሌሎች መስጂዶችና ከተሞች የቀጠለ በመሆኑ የነሱ መፈታት ተጽእኖ ሊኖረው ስለሚችል የዋስትና መብታቸው ይከልከልልኝ›› ብሎ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ‹‹አቃቤ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል፤ የዋስትና መብት ከልክለናል፤ ከፈለጋችሁ ይግባኝ ማለት ትችላላችሁ›› በማለት እጅግ ህገ ወጥ ውሳኔ በመወሰን ምስክር መስማቱን ቀጠለ!
እንግዲህ በዚህ ሂደት ውስጥ እያሉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ህጉን ‹‹የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቅጽ 2/2006›› በሚል አርእስት አሻሽሎ ጥቅምት 1 – 2006 ተግባራዊ አደረገው፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረትም በተማሪዎቹ አንቀጽ (257/ሀ) የተከሰሰው ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ሊቀጣ የሚችለው ከ 10 ቀን እስከ 10 ወር በሚደርስ እስራት ወይም የጉልበት ስራ መሆኑን ያትታል፡፡ ተማሪዎቹ ደግሞ እስከ 10 ወር እስራት ላይ በማሳለፋቸው የዋስትና መብት መሰጠት አይበዛባቸውም ማለት ነው፡፡
በመሆኑም የዋስትና ይግባኝ ጥያቄያቸው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገብቶ ለጥቅምት 25 እና 26 ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ በቀጠሮዎቹም ‹‹ቀድሞውኑ ዋስትና በማያስከለክል አንቀጽ ተከሰው ሳለ መከልከላቸው አግባብነት አልነበረውም፤ የተሰሙት ምስክሮችም በክስ ማመልከቻው ላይ የተጠቀሰውን ጭብጥ ያስረዱ አይደሉም፤ አሁን ደግሞ ወንጀል ግለሰባዊ በመሆኑ አንድ ተከሳሽ ሊጠየቅ የሚገባው ራሱ በሰራው ስራ ብቻ መሆኑ በህግ ተቀምጦ እያለ ውጭ ላይ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ደንበኞቻችን ዋስትና መከልከላቸው ተገቢ አይደለም፤ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዚሁ አመት ባወጣው የቅጣት አወሳሰን መሰረት ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳ ሊቀጡ ከሚችሉት በላይ ታስረዋል፤ በዚህ ላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ የዋትና መብታቸው ይከበር›› ሲሉ የተማሪዎቹ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ አስረዱ፡፡ ፍርድ ቤቱም ለአርብ ጥቅምት 29-02-2006 ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ጥቅምት 29 በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰራው ድራማ ግን እጅግ የሚደንቅ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ‹‹ዛሬ ጠርተናችኋል እንዴ?›› በማለት ነበር ውሳኔውን በግልጽ ለመናገር መወዛገቡን ያሳየው፡፡ በዚያችው አጋጣሚ ከመዝገብ ቤቱ የውስጥ ሰው የተገኘው መረጃ ግን ‹‹የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል›› የሚል ነበር – የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማለት ነው፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የወሰናችሁትን ውሳኔ ከመዝገብ ቤቱ ማረጋገጥ ችለናል፤ ለምን በግልጽ አትነግሩንም?›› በማለት የዳኛውን ከንፈር አደረቁት፡፡ ዳኛው ግን ‹‹አይ… በቃ… ዛሬ ከሰአት አይተነው ውሳኔው ሰኞና ማክሰኞ በጽህፈት ቤት በኩል ይደርሳችኋል›› በማለት ውሳኔው ገለልተኛ አለመሆኑን አሳብቆ አረፈው፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ራሱ ያወጣውን መመሪያ ተቃርኖ (ረስቶት ነው እንኳ አንዳይባል በዚሁ አመት ጥቅምት ላይ ያወጣው ነው) ለጭቁኖቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቦታ የሌለው መሆኑን አሳይቷል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን በዚያው ቀን ከሰአት ውሳኔው ከመዝገብ ቤት እንዲሰወር የተደረገ ከመሆኑም በላይ የውሳኔው ግልባጭም እስካሁን ለተከሳሾች ያልደረሳቸው መሆኑ ነው፡፡
አሁን ተማሪዎቹ ያለባቸው 28 መልካቸውን እንኳ ለይተው የማያውቋቸው የሀሰት ምስክሮች ትርኪ ምርኪ ምስካሬ ቢሆንም ከ20 በላይ ምስክሮች ተሰምተዋል፡፡ የተወሰኑትን አቃቤ ህግ ‹‹የተለየ ነገር አያሰሙልኝም›› በሚል ትቷቸዋል፡፡ አንድ ምስክር ብቻ ቀርቷል፡፡ ለሱ ሲባል ነው እንግዲህ ለህዳር 17-03-2006 ማክሰኞ ከሰአት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሰጠው፡፡
የሀገሪቱ የፍትህ ድብብቆሽ ይህን ይመስላል! ተማሪዎች ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ነው! በአገሪቱ ፍትህ የለምን?
Photo: ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ18ቱን የዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የዋስትና መብት ክልከላ!
ከ2005 አጋማሽ በኋላ የአወልያ ግቢን መሰረት ያደረገውንና 2004 ታህሳስ ወር የተጀመረውን የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መረከብ እንዳለባቸው የሚያስረዱ ጥሪዎች ከየአቅጣጫው ይሰሙ ጀመር፡፡ ይህ አስፈሪ አቅጣጫ ልቦናው ውስጥ ከፍተኛ ፍርሀት የፈጠረበት የኢህአዴግ መንግስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በራሳቸው ጉዳይ (በሰላትና ሂጃብ ጉዳይ) እንዲጨናነቁ በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ እንዳይሳተፉ ለመግታት ማሰቡን ከአንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን የወጣ መረጃ አመለከተ፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ በጥር ወር 2005 መጀመሪያ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊኖር የሚገባውን የአለባበስ፣ አመጋገብና አምልኮ ስነ-ስርአት አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር አውጥቶት የነበረውን ኢ-ህገ መንግስታዊ ረቂቅ ደንብ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ተግባራዊ አደረገ፡፡ ይህ ገና በውይይት ላይ የሚገኝ ረቂቅ ደንብ ምንም እንኳ ሁሉንም የሃይማኖት ተከታዮች የሚመለከት ቢመስልም ቅሉ ግን ያነጣጠረው ድሮም በእናት አገሩ ኢትዮጵያ ፍዳውን እያየ በኖረው ሙስሊም ተማሪ ላይ ነበር፡፡ በውስጡም ሂጃብንና ሰላትን የሚገድቡ ህገ ወጥ ኢህአዴጋዊ ሴራዎች የተጎነጎኑበት ነበር፡፡
በሂደትም 13 የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኒቃብ ለባሽ እህቶች በይፋ እንዲባረሩ ተደረገ፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀመዓ አጠቃላይ አሚር ተባረረ፡፡ በወቅቱ የተፈጠረውን ውዝግብ ያባብሳሉ ተብለው የሚታሰቡ 12 ሙስሊም ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተለጠፈላቸው፡፡ በግቢው የጀመአ ሰላት የሚሰገድባቸው ንብረቶች ተዘረፉ፡፡ ኒቃባቸውን አውልቀው እንዲማሩ፣ ወይም ዊዝድሮዋል ሞልተው ወደቤታቸው እንዲሄዱ፣ አለበለዚያ ግን እንደሚባረሩ አስከፊ ምርጫ የተሰጣቸው ሙተነቂብ እህቶች ‹‹አናወልቅም፤ እንማራለን›› በማለታቸው በዩኒቨርሲቲው ፖሊሶችና የተማሪዎቸ የመኝታ አገልግሎት ሀላፊዎች ከነሻንጣቸው እንደባእድ ከግቢው ውጭ ተወረወሩ፡፡ ተሰብስበው ሲሰግዱ የታዩ 28 ሴት ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡ ጭራሽ ‹‹100 ሜትር ተራርቃችሁ መስገድ አለባችሁ›› እስከመባልም ተደረሰ!
የረቂቅ ደንቡን ህገ ወጥነት ከኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሀይማኖታዊ ድንጋጌዎች አንጻር፣ ከአለም አቀፍ ህግጋት አኳያ፣ ኢትዮጵያ ‹‹ፈለጋቸውን ተከትያለሁ›› ከምትላቸው ሴኩላር አገራት ተሞክሮ አንጻር፣ እንዲሁም ለሰላትና ሂጃብ ኢስላም ከሚሰጠው ቦታ አንጻር መንግስት ባዘጋጃቸው የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ ያስረዳው መላው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ (ክርስትያኖችንም ይጨምራል) በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህገወጥ እርምጃ ቁጣውን መግለጽ ጀመረ፡፡ ጾም፣ ፔቲሽን፣ የገንዘብና የሞራል ድጋፍ፣ ሌላም ሌላም ተደርጎ በዩኒቨርሲቲው ተቃውሞ ተጧጧፈ፡፡
ቁጥራቸው ከ700 እስከ 1200 የሚደርሱ የባህር ዳር ሙስሊም ተማሪዎች ‹‹ሃይማኖታችን እስትንፋሳችን በመሆኑ ካለሱ መኖር አንችልም!›› በማለት ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡ የዚህ ሁሉ የተማረ ሀይል ትምህርት መስተጓጎል ያላሳሰበው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር (መንግስት) ‹‹ሰላት ኦክስጅናችን ነው ብለዋል፤ እስቲ ይሞቱ ከሆነ እናያለን!›› ብሎ ከማሾፍ አንስቶ ተመልሰው ትምህርታቸውን የማይቀጥሉ ከሆነ ለተፈጠረው ችግር ሀላፊነቱን እንደማይወስድ፣ ‹‹አንዳንድ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ለማስተዳደር ያወጣውን ደንብ አንቀበልም በማለት ትምህርት ማቋረጣቸው ይታወቃል›› የሚል የተጻፈበትን ዛቻ አዘል ማስታወቂያ በመለጠፍ ድሮም አላማቸው የተማረውን ሙስሊም ወጣት ከትምህርት ማደናቀፍ መሆኑን አሳበቀ፡፡
በዚህ ክስተት ማግስት ነው እንግዲህ የተማሪዎች እስር የተጀመረው፡፡ መንግስት በየዩኒቨርሲቲዎች ይህንን ተቃውሞ (የህዝበ ሙስሊሙንም የተማሪውንም) ‹‹እያቀጣጠሉብኝ ነው›› ብሎ ያሰባቸውን 17 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና አንድ ሌክቸረር ከየዩኒቨርሲቲው በመልቀም የግፍ ማእከሉ በሆነው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) በየተራ አጎራቸው፡፡ በምርመራው ሂደትም ‹‹ፖሊስ›› ተማሪዎቹን ‹‹ሁሉንም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት ያለሙ ናቸው፤ ምናልባትም ከግብጽና ሳኡዲ መንግስት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው አይቀርም፤ ግብረ አበሮቻቸው ከኢትዮጵያ የወጡ በመሆኑ መንግስት ከጎረቤት አገሮች ጋር ተነጋግሮ ለመያዝ በውይይት ላይ ነው፤ የቴክኒክ ማስረጃዎችን እያሰባሰብን ነው፤ ሂደታቸው በፍርድ ቤት እየታየላቸው ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ራእይና አላማ ለማስቀጠል ሲንቀሳቀሱና ተማሪውን ለሁከት ሲያነሳሱ የነበሩ ናቸው፤ ተማሪዎችን ለጂሀድ ጦርነት ሲያዘጋጁ ነበር…›› ወዘተ በማለት ቀኑን ሙሉ ያለከልካይ በሚፈነጭበት አራዳ ፍርድ ቤት በሽብርተኝነት ከሶ ለአራት ወራት ሲያመላልሳቸው ቆይቷል፡፡
ከአራት ወራት የምርመራ ቆይታ በኋላ አምስቱ (4 ወንድ 1 ሴት) ተለቀው 13ቱ ደግሞ (12 ወንድና 1 ሴት) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት የሽብርተኝነቱን አንቀጽ በመቀየር የወንጀል ህጉን አንቀጽ 32/1/ሀ፣ 38/1 እና 257/ሀ ተላልፈዋል በማለት ከሷቸዋል፡፡ እንግዲህ ልጆቹ ሽብርተኛ ሳይሆኑ ነው ያን ያህል ካንገላቷቸው በኋላ የሽብርተኝነት ክሱን የተዉት! አዲሱ ክሳቸው በጥቅሉ ‹‹የትምህርት ሚኒስቴርን ረቂቅ ደንብ ተግባራዊነት አደናቅፈዋል፤ ራሳቸውን የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በማለት የሰየሙትን ግለሰቦች በሃይል ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል›› የሚል ሆነ፡፡
በሂደት 4ኛ ወንጀል ችሎት ይህንን ጉዳይ የማየት ስልጣን የሌለው መሆኑን ገልጾ በ14ኛ ወንጀል ችሎት በአንድ ዳኛ ብቻ እንዲታይ ተደረገ፡፡ ተማሪዎቹም እንደህግ የተከሰሱበት አንቀጽ ዋስትና የማያስከለክል በመሆኑ የዋስ መብታቸው ተፈቅዶ ጉዳያቸውን በውጪ እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱን ጠየቁ፡፡ እጅግ የሚገርሙ ትርኪ ምርኪ ምክንያቶችን በመደርደር ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን ለመወሰን ብቻ 15 የሚደርሱ ቀጠሮዎችን ሰጥቷል፡፡ በምሳሌነት ብናይ፡-
*ሰኔ 10-10-2005 ‹‹የክስ መቃወሚያ እንስማ›› በሚል ለዋስትና ሌላ ቀጠሮ ተሰጠ፤
*ሰኔ 17-10-2005 ‹‹አልደረሰልንም፤ ምን የሚያጣድፍ ነገር አለ?›› ተባለ፤
*ሰኔ 19-10-2005 ‹‹አልደረሰልንም፤ ሌላ ሪፈር የምናደርገው ነገር አለ›› ተባለ፤ (የአለቆቹን እነ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያምን ተጽእኖ ሪፈር ለማድረግ ይሆን?)
*በሌላ ቀጠሮ ደግሞ ‹‹በቃ በሚቀጥለው ሳምንት ቁርጣችሁን እናሳውቃችኋለን›› ተብሎ ተቀጠረ፤
*ሐምሌ 05-11-2005 ‹‹ከምስክር ጋር አብረን እናየዋለን›› ተባለ፤
በዚህ መልኩ ብዙ እንዲመላለሱ ከተደረገ በኋላ ከ2005 የኢድ ተቃውሞ በኋላ በነበራቸው ቀጠሮ አቃቤ ህግ ‹‹ልጆቹ የተያዙበት እንቅስቃሴ አሁንም በሌሎች መስጂዶችና ከተሞች የቀጠለ በመሆኑ የነሱ መፈታት ተጽእኖ ሊኖረው ስለሚችል የዋስትና መብታቸው ይከልከልልኝ›› ብሎ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ‹‹አቃቤ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል፤ የዋስትና መብት ከልክለናል፤ ከፈለጋችሁ ይግባኝ ማለት ትችላላችሁ›› በማለት እጅግ ህገ ወጥ ውሳኔ በመወሰን ምስክር መስማቱን ቀጠለ!
እንግዲህ በዚህ ሂደት ውስጥ እያሉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ህጉን ‹‹የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቅጽ 2/2006›› በሚል አርእስት አሻሽሎ ጥቅምት 1 – 2006 ተግባራዊ አደረገው፡፡ በዚህ መመሪያ መሰረትም በተማሪዎቹ አንቀጽ (257/ሀ) የተከሰሰው ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝ ሊቀጣ የሚችለው ከ 10 ቀን እስከ 10 ወር በሚደርስ እስራት ወይም የጉልበት ስራ መሆኑን ያትታል፡፡ ተማሪዎቹ ደግሞ እስከ 10 ወር እስራት ላይ በማሳለፋቸው የዋስትና መብት መሰጠት አይበዛባቸውም ማለት ነው፡፡
በመሆኑም የዋስትና ይግባኝ ጥያቄያቸው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገብቶ ለጥቅምት 25 እና 26 ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ በቀጠሮዎቹም ‹‹ቀድሞውኑ ዋስትና በማያስከለክል አንቀጽ ተከሰው ሳለ መከልከላቸው አግባብነት አልነበረውም፤ የተሰሙት ምስክሮችም በክስ ማመልከቻው ላይ የተጠቀሰውን ጭብጥ ያስረዱ አይደሉም፤ አሁን ደግሞ ወንጀል ግለሰባዊ በመሆኑ አንድ ተከሳሽ ሊጠየቅ የሚገባው ራሱ በሰራው ስራ ብቻ መሆኑ በህግ ተቀምጦ እያለ ውጭ ላይ እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ደንበኞቻችን ዋስትና መከልከላቸው ተገቢ አይደለም፤ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዚሁ አመት ባወጣው የቅጣት አወሳሰን መሰረት ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳ ሊቀጡ ከሚችሉት በላይ ታስረዋል፤ በዚህ ላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በመሆናቸው ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ የዋትና መብታቸው ይከበር›› ሲሉ የተማሪዎቹ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ አስረዱ፡፡ ፍርድ ቤቱም ለአርብ ጥቅምት 29-02-2006 ለውሳኔ ቀጠሮ ሰጠ፡፡
ጥቅምት 29 በጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰራው ድራማ ግን እጅግ የሚደንቅ ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱ ‹‹ዛሬ ጠርተናችኋል እንዴ?›› በማለት ነበር ውሳኔውን በግልጽ ለመናገር መወዛገቡን ያሳየው፡፡ በዚያችው አጋጣሚ ከመዝገብ ቤቱ የውስጥ ሰው የተገኘው መረጃ ግን ‹‹የሥር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል›› የሚል ነበር – የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ለማለት ነው፡፡ ተማሪዎቹ ‹‹የወሰናችሁትን ውሳኔ ከመዝገብ ቤቱ ማረጋገጥ ችለናል፤ ለምን በግልጽ አትነግሩንም?›› በማለት የዳኛውን ከንፈር አደረቁት፡፡ ዳኛው ግን ‹‹አይ… በቃ… ዛሬ ከሰአት አይተነው ውሳኔው ሰኞና ማክሰኞ በጽህፈት ቤት በኩል ይደርሳችኋል›› በማለት ውሳኔው ገለልተኛ አለመሆኑን አሳብቆ አረፈው፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ራሱ ያወጣውን መመሪያ ተቃርኖ (ረስቶት ነው እንኳ አንዳይባል በዚሁ አመት ጥቅምት ላይ ያወጣው ነው) ለጭቁኖቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቦታ የሌለው መሆኑን አሳይቷል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን በዚያው ቀን ከሰአት ውሳኔው ከመዝገብ ቤት እንዲሰወር የተደረገ ከመሆኑም በላይ የውሳኔው ግልባጭም እስካሁን ለተከሳሾች ያልደረሳቸው መሆኑ ነው፡፡
አሁን ተማሪዎቹ ያለባቸው 28 መልካቸውን እንኳ ለይተው የማያውቋቸው የሀሰት ምስክሮች ትርኪ ምርኪ ምስካሬ ቢሆንም ከ20 በላይ ምስክሮች ተሰምተዋል፡፡ የተወሰኑትን አቃቤ ህግ ‹‹የተለየ ነገር አያሰሙልኝም›› በሚል ትቷቸዋል፡፡ አንድ ምስክር ብቻ ቀርቷል፡፡ ለሱ ሲባል ነው እንግዲህ ለህዳር 17-03-2006 ማክሰኞ ከሰአት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ የሰጠው፡፡
የሀገሪቱ የፍትህ ድብብቆሽ ይህን ይመስላል! ተማሪዎች ‹‹የፍትህ ያለህ!›› እያሉ ነው! በአገሪቱ ፍትህ የለምን?

በወያኔ ስርዓት ውስጥ በሙስና ያልተጨማለቀ ሰው ቢኖር እኔ ነኝ ዓሉ ወ/ሮ አዜብ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው። “የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው…ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
…….” ተከሳሾቹ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ። መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው። አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል። 26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥ በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው። ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል። ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል። ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።
እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል። 1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል። 2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።
3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ነው ::!!!!!!!!!!!!

   የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ነው
PDF Print E-mail Written
by Administrator Wednesday, 04 December 2013 12:54
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በወያኔው ታጣቂ ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ሲሆን በተሰለፈባቸው አውደ ውጊያዎችም ላይ ከፍተኛ ድል በመቀዳጀት ወታደራዊ የበላይነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡ ለአምባገነናዊ ሥርዓት መንኮታኮት ፍቱን መድሃኒቱ የትጥቅ ትግል መሆኑን የተረዳው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍሎች በተለያዩ ግንባሮች በመንቀሳቀስ ህዝብንና ሀገርን በማሸበርና በማሰቃየት ተግባር ተመድበው ሕብረተሰቡን ቀፍድዶ በመያዝ አንገቱን ቀና አድርጐ እንዳይራመድ በማድረግ ወያኔያዊ ተልዕኮ ያነገቡ የታጠቁ ሃይሎች ላይ ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ የግንባሩ ሠራዊት ኢትዮጵያዊ ኩራት መሆኑን በተጨባጭ እያሳየ ሲሆን በህዳር 24 ቀን 2006 ዓ/ም በታች አርማጭሆ ልዩ ስሙ ዕምባ-ጓዳ በተባለው ቦታ መሽጐ በነበረው የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድን ላይ በሰነዘረው ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ ሃያ አንድ (21) የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድኖችን ገድሎ ሃያ ሰባት (27) ያቆሰለ ሲሆን በዚሁ ዕለት በተካሄደው ውጊያ የተለያዩ ከባድና ቀላል መሳሪያዎች ከነመሰል ጥይቶቻቸው ጭምር መማረካቸውንና ከዚሁ ጥቃት ሰለባ ያመለጡት የልዩ ኃይል ታጣቂ ቡድን አባላት ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት መቋቋም ተስኗቸው እግሬ አውጪኝ በማለት መሣሪያና ትጥቃቸውን እያዝረከረኩ ለመፈርጠጥ ተገደዋል።
Image

Sunday, December 1, 2013

የህዝባችን መከራ የወያኔ የፖለቲካ መጠቀሚያ አይሆንም! (ግንቦት 7)

Ginbot 7 weekly editorial

በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሁንም መከራና ስቃይ ላይ ናቸው። የደረጃ ጉዳይ ነው እንጂ ችግሩ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የተንሰራፋ ነው። በመላው አለም ተበትኖ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ካለማቋረጥ ያደረገው ወገንና ሀገር አኩሪ ጩኸትና አቤቱታ ችግሩ በአለም ዙሪያ ትኩረት እንዲያገኝ ባያደረግ ኖሮ የወገኖቻችን መከራ ከዚህም በከፋ መልክ ይቀጥል እንደነበር ጥርጥር የለውም። አንድ ቀን እንኳን ለሚገዛው ህዝብ ሀላፊነትና ተጠያቂነት ተሰምቶት የማያውቀው የወያኔ ጉጅሌ መንግስት እግሩን እየጎተተ ቢሆንም ወደ ችግሩ አቅጣጫ እንዲመለከት የተገደደው በዚሁ የወገን ጩኸት መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ስላልቻለ ነው እንጂ ይህንን ከአለም አጽናፍ እስከ አለም አጽናፍ ያስተጋባ የወገን ደራሽ ድምጻችንን አዲስ አበባ ላይ እንደ አደረገው በሃይል ለማፈን ወደኋላ አይልም ነበር።
ሀፍረት የለሾቹ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች ይህን የተጋለጠ ሀገርና ህዝብ አዋራጅ ተግባራቸውን እና በውሸት የተበከለ ገመናቸውን ለመሸፈን ከዚያም አልፈው የዋሆችን በማታለል የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የተለመደ ቲያትር መስራቱን ተያይዘውታል። ቴዎድሮስ አድሃኖም ችግሩ ባለበት በሳውዲ መሬት ላይ ሳይሆን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በራሱ ወጪ አሳፍሮ ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ባፈሰሳቸው ኢትዮጵያውያን መሃል እየተጎማለለ ያዛኝ ቅቤ አንጓች ቲያትሩን ሲሰራ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይታይበትም።
እነዚሁኑ ወደ ሀገር የተመለሱ አእምሯቸው በችግር የተመሰቃቀለ ዜጎች ወደ ካሜራ እየገፉ ስለ ሳውዲ ኤምባሲያቸውና ስለመንግስታቸው ‘ድንቅ” አገልግሎት እንዲናገሩ ያስጠኗቸውን ተመሳሳይ አረፍተ ነገር መስማት የሚያሳዝን ባይሆን ኖሮ ተወዳዳሪ የሌለው ኮሜዲ ይወጣው ነበር።Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus, the Minister of Foreign Affairs of Ethiopia.
እውነቱ ዛሬ በሀገራችን የሰፈነው ስደትና አብሮት የሚመጣው መከራ ሁሉ ዋናው አምራች ፋብሪካ ወያኔ መሆኑ ነው። ወያኔ የገነባው ጥቂት ጀሌዎቹንና ሎሌዎችን ተጠቃሚ ያደረገና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በተለይ ወጣቱ በሀገሩ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደረገው ስርአት ነው። የስደታችንና የመከራችን ምንጭ ስደት የሚመጣው በሀገር ተስፋ መቁረጥ ነው። እንጀራ ፍለጋና ጭቆናና አፈና ሽሽት አምልጠን በየባዕድ ሀገሩ እንድንከራተት የሚያደርገን የወያኔ ስርአት ነው። በታሪካችን ውስጥ ተሰደን በባዕድ የተዋረድነው በወያኔ ምክንያት ነው።
በሀገር ውስጥ በአፈና ስር ሆናችሁ፣ በውጪው አለምም በየኢምባሲው የምታሰሙት ጩኸትና የምታፈሱት እምባ እብሪትና ትእቢት ያደነደነውን፣ ዝርፊያ ያደነዘዘውን የወያኔን ልብ እንደማያሸብረው ማወቅ አለብን።
የወያኔ ሹማምንቶች ይግረማችሁ ብለው ከአላንዳች ሀፍረት ያውም በሳውዲ አረቢያ ወጪ ተጓጉዘው ሀገር የገቡትን ግራ የተጋቡ ስደተኞች ለፖለቲካቸው ማሳመሪያ በቴሌቪዥን ስእልና ፎቶግራፍ መነሻ ሲያደርጉትና ለፖለቲካ ስራ መሳሪያ ሲያውሉት እያየን ነው። በነሱ ቤት ብልጥ ፖለቲከኞች መሆናቸው ይሆናል። በኛ ቁስል ላይ እንጨት እየሰደዱ መሆናቸውን ግን ፈጽሞ አይሰማቸውም።
ወያኔ በመካከለኛው ምስራቅ ተሰደው ለፍተው የሚኖሩት ወገኖቻችን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ያውቃል። ቢያንስ በየኢምባሲው ያስቀመጣቸው ነጋዴዎች ይነግሩታል። ችግሩን እንዳላየና እንዳልሰማ የሚያየው ከዜጎች ይልቅ እነሱ አፈር ግጠው ለፍተው ለሚያመጧት የውጪ ምንዛሬ የበለጠ ፍቅር ስላለው ነው። በዚህ ተግባሩ ወያኔ ወገኑን የሸጠ ባሪያ ፈንጋይ ነጋዴ እንጂ የመንግስት መሪ መሆኑ ያጠራጥራል።
ግንቦት 7 የፍትህና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ዘወትር እንደሚለው ሁሉ ይህ የዜግነትና የሀገር ውርደት፣ ይህ ሁሉ የወገን መከራ የሚቆመው የዚህ ሁሉ መሰረት የሆነው ወያኔና ስርአቱ ከመሰረቱ ሲነቀልና ሲወገድ መሆኑን ላፍታም አይዘነጋውም።
እንባችን የሚደርቀው ደማችን በየቦታው መፍሰሱ የሚቆመው መብታችን እንደዜጋ ተከብሮ ቀና ብለን የምንሄድበት ሀገር በትግላችን የተቀዳጀን ጊዜ ብቻ ነው።
ግንቦት 7ን ተቀላቀሉ በያላችሁበት ግንቦት 7 ሁኑ!! እኛ ከዚህ ውርደት ሞቶ የሚገኘው ነጻነት ይሻላል ብለን የተነሳን ልጆቻችሁ ነን። እርሰዎስ?
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ተዋርደን አንቀርም!!! ኢ/ር ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር)

ethiopia


ሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ግፍና በደል በሰላማዊ ሰልፍ ለመቃወም ፓርቲያችን በወሰነው መሰረት ለሚመለከተው ክፍል አሳውቀን ነበር፡፡ መቸም ህዝባችን በጭቆና ውስጥ ስለኖረ በመብቱና በግዴታው መሀል ያለውን ድንበር በውል ካለመረዳቱ የተነሳ ሰልፉ እንዲደረግ ስለመፈቀዱ በተደጋጋሚ ስንጠየቅ ነበር፡፡ ህጉ የሚለው ግን ማስፈቀድ ሳይሆን ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ በተቃራኒው መንግስት በተለያዩ ጉዳዮች ሳቢያ በእለቱ ለሰላማዊ ሰልፉ የደህንነት ከለላ መስጠት የማይችልበት ሁኔታ ከገጠመው ሰልፉን ለጠራው አካል ችግሩን ገልጾ ቀኑ እንዲተላለፍለት ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም ይህን መሰል ጥያቄ ከሚመለከተው መስሪያ ቤት ለፓርቲያችን ባለመቅረቡ በሙሉ ልብ ቅድመ-ዝግጅት ማድረጉን ተያያዝን፡፡ ሁሌም ቢሆን መንግስት ሰበብ ፈልጎ ሊወነጅለንና ከመስመር ሊያስወጣን እንደሚፈልግ በሚገባ እናውቃለንና በጥቃቅን ጉዳዮች ላይ ሳይቀር ጥንቃቄ እናደርጋለን፡፡ ለሚመለከተው መስሪያ ቤት ባሳወቅን በአስራ ሁለት ሰአታት ውስጥ ምላሽ ስላልመጣ ሙሉ በሙሉ ህጋዊነታችንን አረጋግጠናል ማለት ነው፣ እነሱ ደግሞ ጠብ-መንጃ በእጃቸው አለና የፈለጉትን ሁሉ ማድረግ ይችላል፡፡
አቶ ሽመልስ ከማል ለሚዲያወች የሰጡትን ፍጹም ከእውነት የራቀ ውንጀላና ሰበብ አዳምጨዋለው፡፡ “ሰላማዊ ሰልፉን ያገድንበት ምክንያት ጸረ-አረብ መፈክሮች ስለነበሩ ነው” ብለዋል፡፡ መጀመሪያ ደረጃ ሰልፉ ገና ከግቢው ፈቅ ሳይል ነው ያፈኑት፣ ሆኖም የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም አንድ በአንድ እየሆንን ወደ ሰላማዊ ሰልፉ መዳረሻ ለመሄድ ስንሞክር የተወሰኑ አመራሮችን አራት ኪሎ አካባቢ ያዙን፣ እነሱ ቀድሞውኑ ሰልፉ እንዳይካሄድ ስለወሰኑ ነው እንጅ ትንሽ እንኳ ተንቀሳቅሶ የሰልፉን ባህሪ ለመገምገም ምንም እድል አልሰጡንም፡፡
ለምሳሌ ሰልፉን እንደምናደርግ ይፋ ባደረግን ማግስት ከራዲዮ ፋና ተደውሎ አንዳንድ ጥያቄዎች ተጠይቄ ነበር፡፡ በቃለ-መጠይቁ ሰላማዊ ሰልፉ በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም እንደምናደርግ ተናግረናል፡፡ ጋዜጠኛው ለሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች መልዕክት ካለ ብሎ በጠየቀኝ ወቅት የሳውዲ አረቢያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ምልክትና ጽሁፍ ሀይማኖትን የሚመለከት በመሆኑ ዜጎች በስሜታዊነት ባንዲራ እንዳያቃጥሉ፣ እነሱ ቢያዋርዱንም እኛ ግን ክብር ያለን ዜጎች ስለሆንን ተቃውሟችንን ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ እንዳለብን ተናግሬ ነበር፡፡ ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት በዚህና በተለያየ መንገድ በማያሻማ ሁኔታ መልዕክት ባስተላልፍም እነሱ ግን ይህን በመቁረጥ አላስተላለፉትም፡፡ እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች ሲደመሩ የአቶ ሽመልስ ከማል ንግግር ነጭ ውሸት መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
ሁለተኛ የአንድ ሀገር መንግስት ዜጎቹ እየተደፈሩ፣ በማጎሪያ ካምፕ በረሀብና በውሃ ጥም፣ ሌላው ቢቀር መጸዳጃ ቤት እንኳ ተከልክለው ፍጹም ከሰውነት ክብራቸው ወርደው እየተበደሉ፣ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ገና ለገና ተቃዋሚ ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ በሚንጸባረቅ ጥላቻና ተቃውሞ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ይበላሽብኛል ብለን መናገር እንችላለን? ሌላው ይቅር አንድ ክፉና ደጉን የለየ ሰው የሚያስበው ጤነኛ ሃሳብ ነው ማለትስ ይቻላል?
ከእገዳው ባሻገር የሚደንቀው ነገር ደግሞ በፓርቲያችን አመራሮችና አባላት ላይ የተደረገው ድብደባ ነው፣ የሆነ ማስተላለፍ የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ የጭካኔያቸውን መጠን እንድናውቅ የሚደበድቡት አቅመ-ደካሞችን፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶችን እየመረጡ በፍጹም አረመኔነት ነበር፡፡ ይህን ተግባራቸውን ስመለከት የደረሱበትን የዝቅጠት ደረጃ መታዘብ ችያለው፡፡ ከፖለቲካ ልዩነትም፣ ከአምባገነንነትም በላይ ሰዎቹ እንደታመሙ ነው ለመረዳት የቻልኩት፣ስር የሰደደ የቁስ ሰቀቀንና የስልጣን ጥም የተጣባቸው፣ ለዚያ ሲሉም የትኛውንም አይነት ውርደት ለመቀበል የቆረጡና የሞራል ልዕልናቸውን ሙሉ በሙሉ ያጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ስነ-ልቦናቸው ክፉኛ ተቃውሷል እንጂ ሀገር እመራለው የሚል ቡድን እንዲህ ያለ ተግባር ይፈጽማል ለማለት እቸገራለው፡፡ በአባላቶቻችን ላይ ክፍኛ ድብደባ ተፈጽሟል፣ እስከዛሬም እግሮቻቸው መራመድ የማያስችላቸው፣ የሚያነክሱ ሰዎች አሉ፡፡ እውነት ለመናገር ይሄ እብደት ነው፡፡ አንዲት እራሷን መከላከል የማትችል ሴትን ለሶስት መደብደብን ከዚህ በተሻለ ልገልጸው አልችልም፡፡
አንድ ማስገንዘብ የምፈልገው ነገር ለኛ ዋናው ጉዳይ የዜጎቹ ህጋዊነት ወይም ህጋዊ ያለመሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ በምንም አይነት መንገድ ሴቶች እየተደፈሩ፣ ወንዶች በየስርቻው እንደ ውሻ ተቀጥቅጠው እየተገደሉ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ታጉረው ይህን ሁሉ መከራ መቀበላቸውን ልንታገሰው፣ ወይም ከህጋዊነት አንጻር እየተራቀቅን ልንመለከተው አንችልም፣ ስለ ህግም ከተወራ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ጭፍጨፋው ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ባላቸው ላይ ጭምር ሲፈጸም እንደነበር አምኗል፡፡
ባለንበት የግሎባላይዜሽን ዘመን የአንዱ ሀገር ዜጋ ካለ ሀገሩ መገኘት አገር ይያዝ የሚያስብል አይደለም፡፡ መውጣት ካለባቸው ጊዜ በመስጠት፣ ከመንግስታቸው ጋር በመነጋገር በዘዴ ነገሩን መከዎን እየተቻለ አንድ ሀገርና መንግስት በሰዎች ላይ እንዲህ የጭካኔ ጥግ የሆነን አቋም ይዘው መንቀሳቀሳቸው ፍጹም ኢ-ሰብአዊነት ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን እንዲህ ያለ አስከፊ ጊዜ የለም፣ እውነቱን ለመናገር ለአገዛዙ ሰዎች የነበረኝ ጭላንጭል ተስፋም አፈር ተደፍቶባታል፣ እንዲህ ግልጽ የሆነ ጭፍጨፋ እየደረሰብን እንኳ በድፍረት ለመናገር አልፈለጉም፡፡ ስለ ኢትዮጵያውያን መገደል ለማውራት ሲፈልጉ ሌላ ሀገር ይጠቅሱና እነሱም እኮ እየተገደሉ ነው ይላሉ፣ ወገን ከምንለው የማህበረሰባችን አካል ይሄን መስማቱ ከጥቃቱ ይበልጥ ያማል፡፡
ለምሳሌ ኢቲቪ ስለ ጉዳዩ ሲያወራ ህገ ወጥ ሊባል የሚችል ድርጊት ተፈጽሟል በማለት ነው፡፡ ተመልከቱ! እንዴት ያለ ባዕድነት ነው? ኢትዮጵያውያን በድህነትም ውስጥ እንኳ ለክብራችን የመሞት ባህሪ አለን፣ ይሄ ከቀደሙት አንጡራ ኢትዮጵያውያን የወረስነውና ዛሬም ያለን ሀብታችን ነው፡፡
ትናንት ፍየል ጠባቂ የነበረ በረኸኛ ይህን ክብራችንን ገፍፎ እንደውሻ ቀጥቅጦ ስርቻ ሲጥለን ያልተቆጣ መንግስት ኢትዮጵያዊ ነው? ከዜጎቹ የወጣና ለህዝቡ የቆመ እውነተኛ መንግስት ከዚህ የበለጠ የሚቆጣበት ጉዳይ ከወዴት ይመጣል? እውነተኛ መንግስት ቢሆን ኖሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሳውዲ ካምፓኒዎችን በሰአታት ውስጥ ማባረር፣ ኤምባሲውን ዘግቶ አምባሳደሩን ማሰናበትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችን ያሳልፉ ነበር፡፡ የሆነው ግን በተቃራኒው ነው፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቴ ሊበላሽ ይችላል ብሎ እኛ ድምጻችን እንዳናሰማ ደበደበን፣ አፈነን፡፡ በግልጽ እንደሚታየው የጥቅም ትስስሩ ነው አፋቸውን ያዘጋቸው፣ ይህች ጥቅማቸው እንዳትቋረጥ በዜጎች ህይዎት መደራደርን መርጠዋል፡፡
ስነ ልቦናቸው የተቃወሰ በመሆኑና ተራ ስስታሞች በመሆናቸው እንጂ ኢንቨስትመንትም ሆነ ዲፕሎማሲ ግብአትነታቸው ለሰው ልጅ ነው፣ እንደ አህያ ሲያፈጋ ከርሞ ሬሳቸውን ለላከ መንግስት እንዴት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመመለስ ይገዳል?እንዴት እንደ ኢትዮጵያ ያለች ታሪካዊትና ለአፍሪካ የነጻነትና የኩራት ተምሳሌት የሆነች ሀገርን እየመሩ እንዴት ትናንት የነዳጅ ዘይት ባቆማቸው እረኞች ስትዋረድ ዝም ይላሉ?!::
እንዴት!
በዜጎች ህይወት የተደራደረው አገዛዝ ማለፉ አይቀርም፣ ለዚህ ጥርጥር የለኝም፡፡ ታሪክ ለመጥቀስ ብዙ ርቀት መሄድ አያስፈልግኝም፡፡ የቅርብ የሰሜን አፍሪካ አምባገነኖች የከፋ ፍጻሜ አለና፡፡ ኢትዮጵያውያን ፍቅርም ጸብም እናውቃለን፣ ሳውዲዎችም የፈጸሙትን ግፍ ማወራረዳቸው አይቀርም፡፡ በዚህ ክፉ ጊዜ ስለሰብአዊ መብት ቆመናል የሚሉ አለም አቀፍ ተቋማት ዝምታን መምረጣቸው እውነተኝነታቸውን ለመመርመር ጥሩ እድል ይሰጠናል፡፡
መንግስት ቢኖረን ኖሮ ይሄ ሁሉ ውርደት ይፈጸምብን ነበር ብየ አላስብም፡፡ በዚህ ሰአት ርዕሰ-መንግስት ብሆን ኖሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልቅ ድርጅት እንደመሆኑ፣ ወደየትኛውም ሀገር የሚደረገውን ጉዞ አቋርጨ ዜጎቸን ማስወጣትን አስቀድም ነበር፡፡ ያሄ ጥቂት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ሊያመጣብን ቢችልም ከከፋው የዜጎች ስቃይ ጋር ግን በአንድ ሚዛን ላይ አይቀመጥም፡፡ የአደጋ መከላከያና ዝግጁነት ኮሚሽን የሚባል ድርጅት አለ፡፡ በዜጎቻችን ላይ ጎርፍና ድርቅ ሲመጣ ብቻ ነው የሚንቀሳቀሰው? ይሄም ሰው ሰራሽ አደጋ ነው ሙሉ ሀይሉን ወደዚህ አዙሮ ሊንቀሳቀስ ይገባው ነበር፡፡
እርግጥ ነው ባቀድነው መሰረት ሰላማዊ ሰልፉ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዳይሆን አድርገውታል፡፡ ጩኸቱ ግን ይቀጥላል… ባለን አቅም ሁሉ አፈናውንም፣ ወከባውንም ተቋቁመን ለዜጎቻችንና ለኢትዮጵያዊነት እንታገላለን፡፡ አገዛዙ ይሄን ሰላማዊ ሰልፍ ሲያፍን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንድ መልእክት አስተላልፏል፣ ይህን መልእክት እንዲያስትላልፍ ማስገደዳችንም ለኛ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የሳውዲ መንግስት ያሻውን ያደርግ ዘንድ የፈቀድኩት እኔ ነኝ፣ በመሆኑም እሱን በመቃወም ግንኙነቴን አታበላሹ ብሎ እርምጃ በመውሰዱ ህዝቡ የነገሩ ቁልፍ የት እንዳለ፣ የአጥቂወቹ በራስ መተማመን ምን ላይ እንደቆመ በጠራ ሁኔታ ለመመልከት እንዲችል ሆኗል፡፡
ይሄ ሁሉ ነገር እየተፈጸመ የተስተዋለ አንድ ነገር አለ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዝምታ እውነተኛ ማንነታቸው፣ እውነተኛ በአገዛዙ ውስጥ ያላቸውን ቦታ ያሳየን ክስተት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እሳቸው በኢህአዲግ እንጂ በኢትዮጵያ ህዝብ የተመረጡ አይደሉም፡፡ ኢህአዲግ የሚናገረው ከሌለ እርሳቸው የሚሉት አይኖርም፡፡ እንደ አንድ ሀገርና ህዝብ መሪ ግን የመኮነንም ሆነ የማጽናናት ቃል ይጠበቅባቸው ነበር፡፡
ባሉበት ቦታ ያስቀመጣቸው ህወሀት ነው፤ ድርጅቱ ደግሞ ይሄን አቋም አልወሰደም፡፡ ስለዚህ እንደሚቆጣቸው ስለሚያውቁ ዝምታን መረጡ፣ ቸልታንም አስበለጡ፡፡ በሀገርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ከዚህ በላይ ሽንፈት ያለ አይመስለኝም፡፡
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
http://www.goolgule.com/we-shall-arise-again/